የተለጠፉ ዜናዎችን እያዩ
የተቋሙን ግቦች መሠረት ያደረገ እቅድ፣ የተቀናጀ አሠራርና ቁርጠኝነት ለዲጂታል ሽግግር ስኬት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
ቆሼ፤ ህዳር 14/2019 ዓ.ም (የማ/ል/ወ/ኢ/ቴ/ጽ/ቤት) – የማረቆ ልዩ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር ቁፋ ሜጤቦ በእስካሁኑ የተቋሙ የእቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ከአጠቃላይ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ኃላፊው በውይይቱ ወቅት እንዳስገነዘቡት፣ ተቋሙ የራሱ የሆኑ ዋና ዋና ግቦች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ ተግባር እነዚህን ግቦች መነሻ በማድረግ መታቀድና በታቀደው መሠረት በተግባር መፈጸም እንዳለበት አመልክተዋል።
ተቋሙ ለዲጂታላይዜሽን ልህቀት መሠረት የሚጥል ቁልፍ ተቋም መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ዲጂታል ሽግግርን በሀገር ደረጃም ሆነ በልዩ ወረዳችን እውን ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት፣ በትብብርና በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በውይይቱ የተሳተፉት የሴክተሩ ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ ሴክተሩ በውስጡ በርካታና የተለያዩ ተግባራትን የያዘ በመሆኑ እነዚህን ሥራዎች በቅንነት፣ በአንድነትና በተቀናጀ መንገድ ማከናወን እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ ለማሳካት የሁሉም አካላት ድጋፍ፣ ተሳትፎና የጋራ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል።
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ፦
https://t.me/mswinto
አስተያየቶች